የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/09 ገጽ 3
  • ትምህርት ለመጀመር ተዘጋጅታችኋል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትምህርት ለመጀመር ተዘጋጅታችኋል?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ልጆቻችሁ ዝግጁ ናቸው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • ወጣቶች—የትምህርት ቤት ሕይወታችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ትምህርቴን ማቋረጥ ይኖርብኛል?
    ንቁ!—2010
  • ወደኋላ አትበሉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
km 8/09 ገጽ 3

ትምህርት ለመጀመር ተዘጋጅታችኋል?

1. ትምህርት ስትጀምሩ ምን አጋጣሚዎች ይከፈትላችኋል?

1 እናንተ ክርስቲያን ወጣቶች አዲስ ገቢም ሆናችሁ አልሆናችሁ በትምህርት ቤት ውስጥ አዳዲስ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ያጋጥሟችኋል ወይም ተጽዕኖዎች ይደርሱባችኋል። በሌላ በኩል ደግሞ ‘ስለ እውነት ለመመሥከር’ የሚያስችል ጥሩ አጋጣሚም ከፊታችሁ ተዘርግቶላችኋል። (ዮሐ. 18:37) ታዲያ ምሥክርነት ለመስጠት በሚገባ ተዘጋጅታችኋል?

2. ትምህርት ለመጀመር ዝግጅት ማድረግ የምትችሉት በምን መንገዶች ነው?

2 ከይሖዋ፣ ከወላጆቻችሁም ሆነ ከታማኝና ልባም ባሪያ በማንኛውም የሕይወታችሁ ክፍል ስኬታማ እንድትሆኑ የሚያስችላችሁን ሥልጠና አግኝታችኋል። (ምሳሌ 1:8፤ 6:20፤ 23:23-25፤ ኤፌ. 6:1-4፤ 2 ጢሞ. 3:16, 17) በትምህርት ቤት ምን ዓይነት ተፈታታኝ ሁኔታዎች ሊያጋጥሟችሁ እንደሚችሉ ከወዲሁ ሳታስቡበት አትቀሩም። ያገኛችሁትን ሥልጠናም ሆነ ትምህርት ቤት የሚያጋጥማችሁን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ምሥክርነት ለመስጠት ዝግጅት አድርጉ። (ምሳሌ 22:3) የወጣቶች ጥያቄ በተባለው መጽሐፍ በሁለቱም ጥራዞች እንዲሁም በንቁ! መጽሔት ላይ በተመሳሳይ ርዕስ በየጊዜው በሚወጣው አምድ ላይ ያሉትን መመሪያዎችና ጠቃሚ ቅዱስ ጽሑፋዊ ሐሳቦች ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታችሁ አስቡባቸው።

3. ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችሏችሁ አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

3 ልዩ የሆነው የአገልግሎት ክልላችሁ በተለያዩ መንገዶች ምሥክርነት ለመስጠት ያስችላችኋል። ሌሎች ግሩም የሆነውን አለባበሳችሁንና አጋጌጣችሁን፣ ባሕርያችሁንና አነጋገራችሁን፣ አብረዋችሁ ለሚማሩት ተማሪዎችና ለመምህራኖቻችሁ የምታሳዩትን አክብሮት፣ ሌላው ቀርቶ የትምህርት ውጤታችሁን ሲመለከቱ በጠንካራ መሠረት ላይ እንደታነጻችሁ ስለሚያስተውሉ “ከሌሎች የተለያችሁ እንድትሆኑ ያደረጋችሁ ምንድን ነው?” ብለው ሊጠይቋችሁ ይችላሉ። (ሚል. 3:18፤ ዮሐ. 15:19) ይህም ምሥክርነት ለመስጠትና ስለ እምነታችሁ ለማስረዳት አጋጣሚ ሊከፍትላችሁ ይችላል። (1 ጢሞ. 2:9, 10) በዚህ የትምህርት ዓመትም ከአንዳንድ ዝግጅቶችና ከዓመት በዓላት ጋር በተያያዘ ፈተና ሊያጋጥማችሁ እንደሚችል የታወቀ ነው። በእነዚህ ሥነ ሥርዓቶች ላይ የማትካፈሉት ለምን እንደሆነ ስትጠየቁ “ሃይማኖቴ ስለማይፈቅድልኝ ነው።” አሊያም “የይሖዋ ምሥክር ስለሆንኩ ነው” ብላችሁ ብቻ ዝም ትላላችሁ ወይስ ይህን አጋጣሚ ተጠቅማችሁ ስለ አፍቃሪው አባታችሁ ስለ ይሖዋ ምሥክርነት ትሰጣላችሁ? ይሖዋ የሚሰጣችሁን መመሪያ ተከትላችሁ ጥሩ ዝግጅት ማድረጋችሁ ለመምህራኖቻችሁ፣ አብረዋችሁ ለሚማሩ ተማሪዎችና ለሌሎች ግሩም ምሥክርነት ለመስጠት ዝግጁ እንድትሆኑ ያስችላችኋል።—1 ጴጥ. 3:15

4. የተሳካ የትምህርት ዘመን እንደሚሆንላችሁ እርግጠኞች መሆን የምትችሉት ለምንድን ነው?

4 ትምህርት ለመጀመር ስታስቡ ትንሽ ፍርሃት ሊሰማችሁ ቢችልም የተሳካ የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ የሚመኙላችሁ የበርካታ ሰዎች ድጋፍ እንደማይለያችሁ አትዘንጉ። በተጨማሪም ልዩ በሆነው የአገልግሎት ክልላችሁ ለሌሎች ጥሩ ምሥክርነት እንደምትሰጡ ስናስብ እኛም እንደ እናንተ ደስ ይለናል። እንግዲያው ደፋሮች በመሆን ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ዝግጁ ሁኑ!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ