የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ነሐሴ 31, 2009 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከሐምሌ 6 እስከ ነሐሴ 31, 2009 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ20 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
1. ወላጆቹን “የሚረግም” ማንኛውም ሰው እንዲገደል የተወሰነው ለምን ነበር? (ዘሌ. 20:9) [w04 5/15 ገጽ 24 አን. 6]
2. ሁሉም እስራኤላውያን ወንዶች በቂጣ በዓል ላይ መገኘት ከነበረባቸው መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውን የገብሱን በኩር የሚሰበስበው ማን ነበር? (ዘሌ. 23:5, 11) [w07 7/15 ገጽ 26 አን. 3]
3. የኢዮቤልዩ ዓመት ለምን ነገር ምሳሌ ነው? (ዘሌ. 25:10, 11) [w04 7/15 ገጽ 26-27]
4. በዘኍልቍ 2:2 ላይ የተጠቀሰው “ምልክት” ለእስራኤላውያን ሃይማኖታዊ ትርጉም ነበረው? [w02 9/15 ገጽ 21 አን. 4]
5. በዛሬው ጊዜ ያሉ የሙሉ ጊዜ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ከጥንት ናዝራውያን ጋር የሚመሳሰል ምን ዓይነት መንፈስ ያሳያሉ? (ዘኍ. 6:3, 5, 6) [w04 8/1 ገጽ 24-25]
6. ሌዋውያን ጡረታ እንዲወጡ ከሚያዘው ሕግ ውስጥ በዛሬው ጊዜ ባሉ የይሖዋ ሕዝቦች ላይ ሊሠራ የሚችለው የትኛው መሠረታዊ ሥርዓት ነው? (ዘኍ. 8:25, 26) [w04 8/1 ገጽ 25 አን. 1]
7. እስራኤላውያን ‘መጎምጀታቸውን’ የገለጹት እንዴት ነበር? በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖች ከዚህ ምን ትምህርት ያገኛሉ? (ዘኍ. 11:4) [w01 6/15 ገጽ 14-15፤ w95 3/1 ገጽ 16 አን. 10]
8. ማርያም ብቻ በለምጽ የተመታችው ለምንድን ነው? ከዚህስ ምን ትምህርት እናገኛለን? (ዘኍ. 12:9-11) [w04 8/1 ገጽ 26 አን. 3፤ it-2 ገጽ 415 አን. 1]
9. ኢያሱና ካሌብ የከነዓን ነዋሪዎችን እንደ “እንጀራ” አድርገው ሲገልጿቸው ምን ማለታቸው ነበር? (ዘኍ. 14:9) [w06 10/1 ገጽ 16 አን. 5፤ it-1 ገጽ 363-364]
10. ዘኍልቍ 21:5 ምን የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ይዟል? [w99 8/15 ገጽ 26-27]