የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በግንቦት ወር አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር አግኝተናል። እንዲያውም ቀጥሎ የቀረበው ሪፖርት እንደሚያሳየው ለሰባት ተከታታይ ወራት ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር አግኝተናል፦
• ኅዳር 2008 8,363
• ታኅሣሥ 8,462
• ጥር 2009 8,517
• የካቲት 8,537
• መጋቢት 8,597
• ሚያዝያ 8,612
• ግንቦት 8,630
‘እድገት’ እንድናደርግ ስለረዳን ይሖዋን እናመሰግነዋለን። (1 ቆሮ. 3:6) አስፋፊዎችና አቅኚዎችም በጣም አስፈላጊ በሆነው በዚህ መንግሥቱን የመስበክ ሥራ አዘውትራችሁ በቅንዓት ስለምትካፈሉ ልትመሰገኑ ይገባል። የተሟላ ሪፖርት አጠናቅረው ለመላክ ላደረጉት ጥረት የጉባኤ ጸሐፊዎችንም ልናመሰግናቸው እንወዳለን። ይህ እድገት ወደፊትም እንዲቀጥል የምታደርጉትን ጥረት እንደምትገፉበት እንተማመናለን።