መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1
“ብዙ ሰዎች ስለ አዳምና ሔዋን የሚናገረው የዘፍጥረት ዘገባ ልብ ወለድ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ሌሎች ደግሞ አዳምና ሔዋን በእርግጥ በሕይወት እንደነበሩ ያምናሉ። እርስዎስ ምን ይላሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ኢየሱስ፣ ስለ አዳምና ሔዋን ምን ብሎ እንደተናገረ ይመልከቱ። [ማርቆስ 10:6-9ን አንብብ።] ይህ ርዕሰ ትምህርት አዳምና ሔዋን በሕይወት እንደነበሩ የሚያሳዩ አንዳንድ ማስረጃዎችን የያዘ ከመሆኑም ሌላ በእነሱ ሕልውና ማመን አለማመናችን ለውጥ እንደሚያመጣ ያስረዳል።” በገጽ 12 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! መስከረም 2009
አንደኛ ዮሐንስ 4:8ን አንብብ። ከዚያም እንደሚከተለው በል፦ “አንዳንዶች አምላክ ክፉ ሰዎችን በገሃነመ እሳት ለዘላለም እንደሚያሠቃይ ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ ይህ ሐሳብ አሁን ካነበብነው ጥቅስ ጋር እንደሚጋጭ ይሰማቸዋል። እርስዎስ ምን ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ርዕሰ ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚያስተምር ይናገራል።” በገጽ 10 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 1
“ሁላችንም በሕይወታችን ውስጥ ችግሮች ያጋጥሙናል። [በአካባቢያችሁ የተለመዱ አንዳንድ ችግሮችን ጥቀስ።] አምላክ እነዚህን ችግሮች እንድንቋቋም የሚረዳን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ኢየሱስ በዚህ ጥቅስ ላይ አምላክ እኛን የሚረዳበትን አንደኛውን መንገድ ገልጿል። [ሉቃስ 11:13ን አንብብ።] ይህ መጽሔት መንፈስ ቅዱስ ምን እንደሆነና እኛን የሚጠቅመን እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ጥቅምት 2009
“በሁሉም ቤተሰቦች ውስጥ ችግር ማጋጠሙ የማይቀር ነው። ቤተሰቦች አስተማማኝና ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ምክር ከየት ሊያገኙ የሚችሉ ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም መዝሙር 32:8ን አንብብ።] ልዩ እትም የሆነው ይህ ንቁ! መጽሔት እያንዳንዱ ቤተሰብ ተግባራዊ ቢያደርጋቸው ጥቅም ሊያገኝባቸው የሚችሉ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎችን ይዟል።”