ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ጥቅምት፦ መጽሔቶች፤ ኅዳር፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ታኅሣሥ፦ ታላቅ ሰው ወይም ከታላቁ አስተማሪ ተማር፤ ጥር፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
◼ በየዓመቱ የሚዘጋጀው የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም ከአሁን በኋላ ከመንግሥት አገልግሎታችን ጋር አባሪ ሆኖ አይላክም። ከዚህ ይልቅ ፕሮግራሙ ለእያንዳንዱ ጉባኤ ሁለት ቅጂ ይላካል። አንደኛው ፕሮግራም መንግሥት አዳራሽ በሚገኘው የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መለጠፍ የሚኖርበት ሲሆን ሌላኛውን ደግሞ የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ፕሮግራም ለማውጣት ይጠቀምበታል። አስፋፊዎች ከዚህ በፊት እንደሚደረገው በየወሩ አንድ የመንግሥት አገልግሎታችን ቅጂ ይደርሳቸዋል። የመንግሥት አገልግሎታችን የየሳምንቱን የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤትና የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም ይዞ ይወጣል።