ታኅሣሥ 28 የሚጀምር ሳምንት
ታኅሣሥ 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 18 (42)
❑ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
lv ምዕ. 7 አን. 10-19፤ በገጽ 81 ላይ የሚገኘው ሣጥን
❑ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 12-15
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
❑ የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 15 (35)
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። “በስብሰባዎቻችን ላይ ለይሖዋ ለመዘመር ተዘጋጅታችኋል?” የሚለውን ርዕስ አንስተህ ሁሉም አዲሱን የመዝሙር መጽሐፋቸውን ከጥር ጀምረው ይዘው እንዲመጡ አበረታታቸው።
10 ደቂቃ፦ መልስ መስጠት ያለብን እንዴት ነው? በክልላችሁ ውስጥ የሚያጋጥሟችሁን የተለመዱ የተቃውሞ ሐሳቦች በተመለከተ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ከእነዚህ የተለመዱ የተቃውሞ ሐሳቦች መካከል አንዱን በመጠቀም አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። (ማመራመር መጽሐፍ ከገጽ 63-67 ተመልከት።)
10 ደቂቃ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ማስጀመር። ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠኑ ግብዣ የምናቀርብበትን ቀጣዩን ቀን ተናገር። በዚህ ረገድ በጉባኤያችሁ ምን ውጤት ተገኝቷል? አንድ አቅኚ ወይም አስፋፊ በክልሉ ውስጥ ይበልጥ ውጤታማ ሆኖ ያገኘውን መግቢያ እንዲናገር አሊያም በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ በጥር ወር የምናበረክተው ጽሑፍ። የሚበረከተውን ጽሑፍ ይዘት በአጭሩ ከልስ። በዚህ ጽሑፍ አማካኝነት መደበኛ ባልሆነ መንገድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር ስለሚቻልባቸው የተለያዩ መንገዶች ከአንድ አስፋፊ ጋር ተወያይ። በዚህ ወር ቢያንስ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ሁሉም ግብ እንዲያወጡ አበረታታ።
መዝሙር 86 (193)