ጥር 11 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥር 11 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 21-24
ቁ. 1፦ ኢያሱ 24:1-13
ቁ. 2፦ አምላክ ለሰዎች ምንም የማያስብና ደንታ ቢስ ነው?
ቁ. 3፦ መጽሐፍ ቅዱስ ሥጋ ከሞተ በኋላ ተነጥላ በሕይወት የምትኖር ነፍስ እንዳለች ይገልጻል? (rs ገጽ 169 አን. 1 እስከ ገጽ 170 አን.1)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻችሁ እንዴት ማጥናት እንደሚችሉ አስተምሯቸው። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 28-31 ላይ “የአጠናን ዘዴ” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር በሚገኙት ሐሳቦች ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ተሞክሮ ያለው አንድ አስፋፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ ገጽ 7 ላይ ተመሥርቶ አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ ለጥናቱ እንዴት መዘጋጀት እንደሚችል ሲያስረዳው በሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ ክፍልህን ጀምር።
15 ደቂቃ፦ “ለመስበክ ብቁ ነኝ?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። በአንቀጽ 4 ላይ ከተወያያችሁ በኋላ ለአንድ አስፋፊ ቃለ መጠይቅ አድርግ። እንደሚከተሉት ያሉ ጥያቄዎችን ጠይቀው፦ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመስበክ ምን ችግሮችን መቋቋም ጠይቆብሃል? በአገልግሎትህ ንቁ እንዲሁም ውጤታማ እንድትሆን ምን እርዳታ አግኝተሃል?