ጥር 18 የሚጀምር ሳምንት
ጥር 18 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መሳፍንት 1-4
ቁ. 1፦ መሳፍንት 2:11-23
ቁ. 2፦ መጽሐፍ ቅዱስ ሲኦል ብሎ ወደሚጠራው ሥፍራ የሚሄዱት ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው? (rs ገጽ 170 አን. 2-4)
ቁ. 3፦ ዲያብሎስ የመጣው ከየት ነው?
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “በጠና የታመሙ ሰዎችን ማጽናናት።” በግንቦት 1, 2008 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 25-29 ላይ ተመሥርቶ በንግግር የሚቀርብ። ክፍሉን የሚያቀርበው ሽማግሌ ምሳሌ 17:17ን በማንበብ ይጀምራል፤ ከዚያም በቀጥታ “በሕመሙ ሳይሆን በግለሰቡ ላይ ትኩረት አድርግ” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ወደሚገኙት አንዳንድ ዋና ዋና ነጥቦች ይሻገራል። በመቀጠል “ለማዳመጥ ዝግጁ ሁን” የሚለውን ንዑስ ርዕስ ሁለተኛ አንቀጽና “አስፈላጊ የሆኑትን መሠረታዊ ነገሮች መረዳት” የሚለውን ንዑስ ርዕስ ሁለተኛ አንቀጽ መሠረት በማድረግ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን መደበቅ ምን ውጤት እንደሚያስከትል ግለጽ። ዕብራውያን 13:18ን እና ኤፌሶን 4:25ን አንብብ። ከዚያም ገጽ 28 ከአንቀጽ 4-6 ላይ እንዲሁም ገጽ 29 ላይ ባለው ሣጥን ውስጥ የሚገኙት ምክሮች ያላቸውን ጥቅም ተናገር። በመጽሔቱ ላይ የሚገኙትን የመደምደሚያ ሐሳቦች በመጥቀስ ውይይቱን ቋጭ።
7 ደቂቃ፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። የመጽሔቶቹን ይዘት በአጭሩ ከተናገርክ በኋላ በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ይበልጥ የሚማርኩት የትኞቹ ርዕሶች እንደሆኑ ሐሳብ ስጥ። አንድ ወጣት አስፋፊ መጽሔቶቹን ለማበርከት እንዴት ዝግጅት እንደሚያደርግ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
8 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱ ጥቅሶችን አንብብና ተወያዩባቸው።