የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በአዲሱ የአገልግሎት ዓመት የመጀመሪያ ወር 8,623 አስፋፊዎች ሪፖርት ያደረጉ ሲሆን ይህ ቁጥር ካለፈው ዓመት አማካይ የአስፋፊዎች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር አንድ በመቶ ጭማሪ ያሳያል። ከእነዚህ አስፋፊዎች መካከል 5,000 የሚያህሉት የሚገኙት በአዲስ አበባ ነው። በአጠቃላይ በአገራችን ለአንድ አስፋፊ 8,649 ሰው የሚደርስ ሲሆን ከአዲስ አበባ ውጪ ግን ለአንድ አስፋፊ 20,000 ሰው ይደርሳል። በዚህ ረገድ መሻሻል እንዳለ የታወቀ ነው፤ ይሁንና ምሥራቹን ያልሰሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን መርዳት የምንችልበትን መንገድ ለማግኘት ንቁ መሆን ያስፈልገናል። በተጨማሪም የመስከረም ወር ፍላጎት ያላቸው ሰዎች በአውራጃ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ለመጋበዝ ባለ ቀለም የመጋበዣ ወረቀቶችን ማሰራጨት የጀመርንበትና ግሩም ውጤት የተገኘበት ወር ነው።