መጋቢት 29 የሚጀምር ሳምንት
መጋቢት 29 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 14-15
ቁ. 1፦ 1 ሳሙኤል 14:24-35
ቁ. 2፦ ወደ ይሖዋ መቅረብ የምንችልባቸው መንገዶች (ያዕ. 4:8)
ቁ. 3፦ ኮከብ ወደ ኢየሱስ የመራቸው ከምሥራቅ የመጡ ጠቢባን ወይም ሰብአ ሰገል እነማን ናቸው? (rs ገጽ 177 አን. 2-4)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ማስጀመር። በሚያዝያ ወር ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምሩ የምንጋብዘው መቼ እንደሆነ ተናገር። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላስጀመረ አንድ አስፋፊ ቃለ ምልልስ አድርግ። በአገልግሎት ክልሉ ውስጥ ውጤታማ ሆኖ ያገኛቸው መግቢያዎች የትኞቹ ናቸው? ተመላልሶ መጠየቅ የሚያደርገው ምን ግብ ይዞ ነው? እሱ ከተጠቀመባቸው መግቢያዎች አንዱን በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ እስከ ዛሬ ከተከናወኑት ሁሉ ታላቅ በሆነው የፍለጋ ሥራ ተካፈሉ! የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ገጽ 95 ላይ “የሚገባቸውን ፈልጎ ማግኘት” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።
10 ደቂቃ፦ “ከቤት ወደ ቤት ስታገለግሉ ጥሩ ረዳት ሁኑ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።