የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
ሦስተኛው ልዩ ዘመቻ በጥር ወር ተጀምሯል። እስከ አሁን ድረስ 28 ወንድሞችና እህቶች ከአምስት የውጭ አገራት የመጡ ሲሆን በአገራችን ከሚገኙ ጉባኤዎች ወደ 400 የሚጠጉ ወንድሞችና እህቶችም ወደተለያዩ ቦታዎች ተመድበዋል። ባለፉት ዓመታት እንደነበሩት ሁሉ ከምድባቸው የተመለሱት ወንድሞች ፍላጎት ያላቸው ሰዎችን በማግኘታቸው በጣም ተደስተዋል።
በዚህ ወር 8,652 አስፋፊዎች ሪፖርት ያደረጉ ሲሆን ይህ አኃዝ ባለፈው ዓመት በነሐሴ ወር ካገኘነው ከፍተኛ ቁጥር የሚያንሰው በትንሹ ነው። በዚህ ወር የነበረው አማካይ ሰዓት 13.1 ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ደግሞ በአማካይ 0.3 ነበር። ይሖዋ 6,262 የሚሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች እንዲባርካቸው ጸሎታችን ነው፤ እንዲሁም ከእነሱ መካከል በመታሰቢያው በዓል ወቅት ይሖዋን ማገልገል የሚጀምሩ እንደሚኖሩ ተስፋ እናደርጋለን። እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? የሚለውን ትራክት እንዲሁም ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ተጠቅመን ጥናት ለማስጀመር ንቁዎች ከሆንን በርካታ ሰዎች የይሖዋ ወዳጆች እንዲሆኑ መርዳት እንደምንችል ምንም ጥርጥር የለውም።