የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
የመጋቢት ወር ልዩ ወቅት ነበር! የአገልግሎት ክልሎችን ለመሸፈን የተደረገው ልዩ ዘመቻ የተጠናቀቀው በዚህ ወር ሲሆን ከመታሰቢያው በዓል ጋር በተያያዘም ተጨማሪ እንቅስቃሴ አድርገናል። በዚህም ምክንያት በሰዓት፣ በተመላልሶ መጠየቅና በአስፋፊዎች ቁጥር ረገድ አዲስ ከፍተኛ ጭማሪ አግኝተናል፤ የአስፋፊዎች ቁጥር 8,804 ደርሷል። ከዚህም በላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን ቁጥር በ350 ጨምሯል፤ ይህ አኃዝ እስከ ዛሬ ካስመዘገብነው ከፍተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ቁጥር ሁለተኛው ነው! በዚህ ወር ያደረጋችሁት እንቅስቃሴ አስደሳች ነበር፤ ወደፊትም በምታገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሰዎችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የምታደርጉትን ጥረት እንድትገፉበት እናበረታታችኋለን!