ነሐሴ 16 የሚጀምር ሳምንት
ነሐሴ 16 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 1-4
ቁ. 1፦ 2 ነገሥት 1:1-10
ቁ. 2፦ ቁሳዊ ንብረት ዘላቂ እርካታ ሊያስገኝ የማይችለው ለምንድን ነው? (መክ. 5:10)
ቁ. 3፦ ዛሬ በብዙ ቦታዎች በሚሠራባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ውስጥ የአምላክ ስም የት ላይ ይገኛል? (rs ገጽ 191 አን. 6 እስከ ገጽ 193 አን. 10)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ ጥናታችሁ አስፋፊ እንዲሆን እርዱት። የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 78 አንቀጽ 3 አንስቶ እስከ ገጽ 80 መጨረሻ ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።
10 ደቂቃ፦ ምሥራቹ ያለውን ጠቀሜታ ማጉላት። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 158 አን. 5 አንስቶ እስከ ገጽ 159 መጨረሻ ድረስ ባሉት ሐሳቦች ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በአገልግሎት ክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን የሚያሳስባቸው ነገር ምን እንደሆነ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ። ሰዎችን የሚያሳስቧቸውን እንደነዚህ ያሉ ነገሮች በመግቢያችን ላይ ልንጠቀም የምንችለው እንዴት እንደሆነ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ “በተገቢው ጊዜ የቀረበ ምግብ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። የሚቀጥለው የልዩ ስብሰባ ቀን የሚታወቅ ከሆነ ተናገር።