ነሐሴ 23 የሚጀምር ሳምንት
ነሐሴ 23 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 1 አን. 12 እስከ ምዕ. 2 አን. 6
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 5-8
ቁ. 1፦ 2 ነገሥት 6:8-19
ቁ. 2፦ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በአምላክ የግል ስም የማይጠቀሙት ወይም በጥቂት ቦታዎች ላይ ብቻ የሚያስገቡት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 194 አን. 1 እስከ ገጽ 195 አን. 2)
ቁ. 3፦ ሥጋዊ ምኞት አምላክ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው? (ፊልጵ. 3:18, 19)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ በመስከረም ወር፣ ሰዎችን በምታነጋግሯቸው በመጀመሪያው ዕለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አስጀምሩ። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በመስከረም ወር የምናበረክተው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ሲሆን የቤቱን ባለቤት በምናነጋግርበት በመጀመሪያው ዕለት ከግለሰቡ ጋር አንድ ወይም ሁለት አንቀጾችን ለመወያየት ጥረት እናደርጋለን። እንዲህ ማድረግ የሚቻልባቸውን መንገዶች ጥቀስ። በተጨማሪም ሰዎችን በምናነጋግርበት በመጀመሪያው ዕለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዴት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳዩ አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
20 ደቂቃ፦ “መደበኛ ባልሆነ መንገድ መመሥከር ትችላላችሁ!”—ክፍል 1። ከአንቀጽ 1-8 ላይ ተመሥርቶ በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። የተሰጡትን አንድ ወይም ሁለት ሐሳቦች በመጠቀም ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።