የ2011 የቀን መቁጠሪያ ለቤተሰብ አምልኮ ትልቅ ትኩረት ሰጥቷል
የ2011 የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ ጭብጥ የቤተሰብ አምልኮ ነው። የቀን መቁጠሪያው በአሁኑ ጊዜ ያሉትንና በጥንት ዘመን የነበሩትን ቤተሰቦች ያሳያል። ከዚህም በተጨማሪ ባልና ሚስቶችና ነጠላ የሆኑ የይሖዋ አገልጋዮች የአምላክን ቃል ሲያጠኑ ያሳያል።
በቀን መቁጠሪያው ላይ የሚታዩት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ሰዎች በይሖዋ ቃል ደስ የሚሰኙ ሲሆን እንዲህ ማድረጋቸው ያጋጠሟቸውን ተፈታታኝ ሁኔታዎች እንዲወጡ ከፍተኛ እርዳታ አድርጎላቸዋል። (መዝ. 1:2, 3) በቀን መቁጠሪያው ላይ ያለውን ሥዕል በትኩረት ስንመለከት፣ ቤተሰባችን ትልቅም ይሁን ትንሽ እንዲሁም የቤተሰቡ አባላት በእምነት አንድ ሆኑም አልሆኑም የቤተሰብ አምልኮ ማድረጋችን ያለውን አስፈላጊነት ያስታውሰናል። የቤተሰብ አምልኮ ለማድረግ ያሰባችሁበትን ቀን እንድትጽፉበት ተብሎ በቀን መቁጠሪያው ላይ ክፍት ቦታ ተዘጋጅቷል። ታዲያ እናንተስ እዚህ ቦታ ላይ ቀኑን ሞልታችኋል?