ታኅሣሥ 27 የሚጀምር ሳምንት
ታኅሣሥ 27 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 25-28
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። “የ2011 የቀን መቁጠሪያ ለቤተሰብ አምልኮ ትልቅ ትኩረት ሰጥቷል።” በንግግር የሚቀርብ።
10 ደቂቃ፦ አስተዋጽኦ ማዘጋጀት በአገልግሎት ላይ የሚጠቅመን እንዴት ነው? በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 166 አንቀጽ 5 እስከ ገጽ 167 አንቀጽ 4 ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። አንድ አስፋፊ ወደ አገልግሎት ከመውጣቱ ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ በሚቀጥለው ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ለማበርከት ስለሚጠቀምበት መግቢያ በአእምሮው ሲያውጠነጥን የሚያሳይ መነባንብ እንዲያቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ሽበት የክብር ዘውድ ነው። (ምሳሌ 16:31) በ2010 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 110 አንቀጽ 1-3 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። በእያንዳንዱ ተሞክሮ ላይ ከተወያያችሁ በኋላ አድማጮች ምን ትምህርት እንዳገኙ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
10 ደቂቃ፦ በጥር ወር መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። በውይይት የሚቀርብ። በአንድ ወይም በሁለት ደቂቃዎች ውስጥ የመጽሔቶቹን ይዘት ከልስ። ከዚያም ሁለት ወይም ሦስት ርዕሰ ትምህርቶችን ምረጥና እነዚህን ርዕሶች ተጠቅሞ መጽሔቶቹን ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዲሁም የትኛውን ጥቅስ ማንበብ እንደሚችሉ አድማጮችን ጠይቅ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።