ጥር 24 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥር 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 53 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 8 አን. 1-11 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዕዝራ 6-10 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዕዝራ 7:1-17 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ኢየሱስ ንጉሥ ሆኖ ለመግዛት ብቃቱ እንዳለው በተግባር ያሳየው እንዴት ነው? (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ራሱ ነው?—rs ገጽ 213 አን. 1-2) (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። ለሚቀጥለው ሳምንት የአገልግሎት ስብሰባ ሁሉም የጥር 1, 2011ን መጠበቂያ ግንብ ይዘው እንዲመጡ ተናገር። በየካቲት ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ከተናገርክ በኋላ አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
20 ደቂቃ፦ “ቤተሰቦችን ለመርዳት የተደረገ ዝግጅት።”—ክፍል 1 (አንቀጽ 1-6 እና በገጽ 6 ላይ የሚገኘው ሣጥን።) በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አድማጮች በገጽ 6 ላይ በሚገኘው ሣጥን ውስጥ ከቀረቡት ሐሳቦች መካከል አንዳንዶቹን በሚቀጥለው የቤተሰብ አምልኮ ምሽት ላይ እንዲጠቀሙባቸው አበረታታ። በሚቀጥለው ሳምንት በቀሩት አንቀጾች ላይ ውይይት ሲደረግ ቤተሰባቸው ምን ጥቅም እንዳገኘ ሐሳብ መስጠት ይችላሉ።
10 ደቂቃ፦ በየካቲት ወር መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። በውይይት የሚቀርብ። በአንድ ወይም በሁለት ደቂቃዎች ውስጥ የመጽሔቶቹን ይዘት ተናገር። ከዚያም ሁለት ወይም ሦስት ርዕሶችን ምረጥና መጽሔቶቹን ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዲሁም የትኛውን ጥቅስ ማንበብ እንደሚችሉ አድማጮችን ጠይቅ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 32 እና ጸሎት