መጋቢት 14 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መጋቢት 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 10 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 9 ከአን. 36-40 እና ከገጽ 149-152 የሚገኘው ሣጥን (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 1-5 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ኢዮብ 3:1-26 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች ከተዉት ምሳሌ ምን ልንማር እንችላለን?—ዘኍ. 36:10-12 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ያደረጋቸው ተአምራት እርሱ እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ያረጋግጣሉ?—rs ከገጽ 216 አን. 4 እስከ ገጽ 217 አን. 2 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ ይሖዋን በማገልገል የሚገኝ ብልጽግና። (ምሳሌ 10:22) በ2010 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ከገጽ 225 አንቀጽ 1 እስከ ገጽ 226 አንቀጽ 2፣ ከገጽ 227-228 እንዲሁም ከገጽ 232 አንቀጽ 1 እስከ ገጽ 233 አንቀጽ 1 ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። በእያንዳንዱ ተሞክሮ ላይ ከተወያያችሁ በኋላ አድማጮች ምን ትምህርት እንዳገኙ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
15 ደቂቃ፦ “አድናቆት እንዳለን እናሳይ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። የመታሰቢያውን በዓል አስመልክቶ ጉባኤው ያደረገውን ዝግጅት ተናገር።
መዝሙር 8 እና ጸሎት