መጋቢት 21 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መጋቢት 21 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 47 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 9 ከገጽ 153-163 የሚገኘው ሣጥን (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 6-10 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ኢዮብ 8:1-22 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ለመዳን የሚያስፈልገው በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ብቻ ነው?—rs ገጽ 217 አን. 4 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ በማቴዎስ 10:16 ላይ የሚገኘውን ምክር ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ መልስ ስትሰጡ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቀሙ። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 143 እስከ 144 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። በአካባቢያችሁ ሊነሳ የሚችል ጥያቄ ለአንድ አስፋፊ ሲቀርብለት የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። በመጀመሪያው ሠርቶ ማሳያ ላይ አስፋፊው ትክክለኛውን መልስ ይሰጣል፤ ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ አይጠቅስም። በሁለተኛው ሠርቶ ማሳያ ላይ ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሞ መልስ ይሰጣል። ሁለተኛው አቀራረብ የተሻለ የሆነው ለምን እንደሆነ ሐሳብ እንዲሰጡ አድማጮችን ጋብዝ።
15 ደቂቃ፦ “የመታሰቢያው በዓል የመጋበዣ ወረቀት ሚያዝያ 2 መሰራጨት ይጀምራል።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። የመታሰቢያው በዓል የመጋበዣ ወረቀት አንድ ቅጂ ለሁሉም አስፋፊዎች እንዲታደል አድርግ፤ ከዚያም ይዘቱን በአጭሩ ከልስ። የጉባኤውን ክልል ለመሸፈን የተደረገውን ዝግጅት ጥቀስ። አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 5 እና ጸሎት