መጋቢት 28 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መጋቢት 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 45 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 10 አን. 1-9 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 11-15 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ኢዮብ 13:1-28 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ኢየሱስ “የሰንበት ጌታ” የሆነው እንዴት ነው?—ማቴ. 12:8 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ሰው ከመሆኑ በፊት በሰማይ ይኖር ነበር?—rs ገጽ 218 አን. 1-2 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። በሚያዝያ ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር፤ ከዚያም አንድ አስፋፊ መጽሔቶችን ላበረከተለት ግለሰብ ተመላልሶ መጠየቅ ሲያደርግ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዴት ማስጀመር እንደሚችል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ በጉባኤም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመንግሥቱን ሥራ መደገፍ። የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 127 እስከ ገጽ 129 አንቀጽ 2 ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።
10 ደቂቃ፦ በሚያዝያ ወር መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። በውይይት የሚቀርብ። በአንድ ወይም በሁለት ደቂቃዎች ውስጥ የመጽሔቶቹን ይዘት ተናገር። ከዚያም ሁለት ወይም ሦስት ርዕሶችን ምረጥና መጽሔቶቹን ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄዎች ማንሳት እንዲሁም የትኞቹን ጥቅሶች ማንበብ እንደሚችሉ አድማጮችን ጠይቅ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ “በአንድ ወቅት የዘወትር አቅኚ ነበርክ?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አቅኚነት አቁሞ የነበረና ሁኔታዎች ሲስተካከሉለት የሙሉ ጊዜ አገልግሎቱን እንደገና የጀመረ አቅኚ (እህትም ልትሆን ትችላለች) ካለ አጠር ያለ ቃለ ምልልስ አድርግለት። እንደገና አቅኚነቱን እንዲቀጥል ያስቻለው ምንድን ነው? ምን በረከቶችስ አግኝቷል?
መዝሙር 6 እና ጸሎት