ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ሚያዝያ እና ግንቦት፦ መጽሔቶች፤ ሰኔ፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ሐምሌ፦ ብሮሹሮች። ቀጥሎ ካሉት ብሮሹሮች ውስጥ ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል፦ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፣ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ነቅተህ ጠብቅ!፣ ሪል ፌይዝ—ዩር ኪ ቱ ኤ ሃፒ ላይፍ (ለሙስሊሞች)፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ዘ ሮድ ቱ ኤቨርላስቲንግ ላይፍ—ሃቭ ዩ ፋውንድ ኢት?፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት እና ሕይወት የተገኘው በፍጥረት ነው?
◼ ጉባኤዎች የአውራጃ ስብሰባቸውን ለማድረግ አንድ ሳምንት ሲቀራቸው በሚያደርጉት የአገልግሎት ስብሰባ ላይ የአውራጃ ስብሰባውን በሚመለከት በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ በወጡት ምክሮችና ማሳሰቢያዎች ላይ መወያየት ይችላሉ። የአውራጃ ስብሰባውን ካደረጉ ከአንድ ወይም ከሁለት ወር በኋላ ደግሞ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት የሚለውን ክፍል ተጠቅመው አስፋፊዎች ለአገልግሎት ጠቃሚ ሆነው ባገኟቸው ሐሳቦች ላይ ውይይት ማድረግ ይችላሉ።
◼ ከግንቦት ወር ጀምሮ ሁሉም ጉባኤዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የየወሩን የመጀመሪያ ቅዳሜ መጠቀም ይኖርባቸዋል። “ከአምላክ ቃል ተማር” የሚለው የመጠበቂያ ግንብ ዓምድ የተዘጋጀው አስፋፊዎች ይህን እንዲያደርጉ ለመርዳት ታስቦ ነው። በመንግሥት አገልግሎታችን የመጨረሻ ገጽ ላይ በመጀመሪያው ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልንጠቀምበት የምንችለውን የመግቢያ ሐሳብ ጨምሮ ለቀጣዩ ወር የሚሆኑ የናሙና አቀራረቦች ይወጣሉ።
◼ በአገልግሎት ላይ የምንጠቀምባቸውን S-4፣ S-8 እና S-43 የመሳሰሉ ቅጾች ለማስቀመጥ የሚያገለግል ከእንጨት የተሠራ አነስ ያለ የቅጾች ማስቀመጫ የሌላቸው ጉባኤዎች እንዲህ ያለውን ማስቀመጫ እንዲያዘጋጁ እናበረታታቸዋለን።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች፦ እንግሊዝኛ፦ ሪል ፌይዝ—ዩር ኪይ ቱ ኤ ሃፒ ላይፍ (ብሮሹር፣ ለሙስሊሞች)፣ ዎችታወር ላይብረሪ በሲዲ፤ ፈረንሳይኛ፦ ዎችታወር ላይብረሪ በሲዲ።
◼ እንደገና የደረሱን ጽሑፎች፦ አማርኛ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ ነቅተህ ጠብቅ!፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፤ እንግሊዝኛ፦ ታላቅ ሰው፣ ጀሆቫስ ዴይ፣ ሮድ ቱ ላይፍ፣ አዲስ ዓለም ትርጉም በኪስ የሚያዝ ዴሉክስ፤ በዲቪዲ፦ ፌይዝ ኢን አክሽን—1፣ ሪስፔክት ኦቶሪቲ፣ ሼር ጉድ ኒውስ፣ ዘ ባይብል፣ ዎርኒንግ ኤግዛምፕልስ፣ ሆል አሶስዬሽን፣ ዎንደርስ ኦቭ ክርኤሽን፤ ፈረንሳይኛ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ ከአምላክ ፍቅር አትውጡ፤ ኦሮምኛ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ ያስባል፣ በደስታ ኑር!፣ አምላክን አምልክ፤ ሲዳምኛ፦ በደስታ ኑር!፤ ትግርኛ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ የሕይወት ዓላማ፤ ወላይትኛ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ የሙታን መናፍስት።