ግንቦት 2 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ግንቦት 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 30 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 11 አን. 21-30 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 38-42 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ኢዮብ 40:1-24 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ገር እና ታጋሽ መሆን የሚያስገኛቸው ጥቅሞች (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ፦ “ኢየሱስን እንደ ግል አዳኝህ አድርገህ ትቀበለዋለህ?”—rs ገጽ 220 አን. 4 እስከ ገጽ 221 አን. 1 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። ወንድሞች በግንቦት ወር በመጀመሪያው ቅዳሜ ሲያገለግሉ በቅርብ የደረሰንን የመጠበቂያ ግንብ እትም ተጠቅመው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዴት ማስጀመር እንደሚችሉ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሁሉም ጥናት ለማስጀመር ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ በግንቦት ወር መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። በውይይት የሚቀርብ። በአንድ ወይም በሁለት ደቂቃዎች ውስጥ የመጽሔቶቹን አንዳንድ ርዕሰ ትምህርቶች ከልስ። ከዚያም ሁለት ወይም ሦስት ርዕሰ ትምህርቶችን ምረጥና እነዚህን ርዕሶች ተጠቅሞ መጽሔቶቹን ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዲሁም የትኛውን ጥቅስ ማንበብ እንደሚችሉ አድማጮችን ጠይቅ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 51 እና ጸሎት