ግንቦት 9 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ግንቦት 9 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 48 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 12 አን. 1-8 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 1-10 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ መዝሙር 7:1-17 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ፦ “ኢየሱስን እንደ ግል አዳኜ አድርጌ ተቀብዬዋለሁ”—rs ገጽ 221 አን. 2 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ኢየሱስ “ጥሩ መምህር” በማለት የጠራውን ሰው ያረመው ለምንድን ነው?—ማርቆስ 10:17, 18 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ ከሰው ይልቅ አምላክን እንደ ገዢያችን አድርገን ልንታዘዝ ይገባል። (ሥራ 5:29) በ2011 የዓመት መጽሐፍ ከገጽ 219 አንቀጽ 4 እስከ ገጽ 221 አንቀጽ 2 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። በእያንዳንዱ ተሞክሮ ላይ ውይይት ካደረጋችሁ በኋላ ምን ትምህርት እንዳገኙ አድማጮችን ጠይቅ።
10 ደቂቃ፦ በእረፍት ጊዜህ ረዳት አቅኚ መሆን ትችላለህ? በውይይት የሚቀርብ። ረዳት አቅኚ ለመሆን የሚያስፈልጉትን ብቃቶች በመግለጽ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 112-113 ያለውን ሐሳብ በአጭሩ ከልስ። በዓመት እረፍታቸው ወይም ትምህርት ቤት ሲዘጋ ረዳት አቅኚ የሆኑ አስፋፊዎች ያገኙትን በረከት እንዲናገሩ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ “ብርሃናችሁ ይብራ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አርዓያ የሚሆን ምግባር ማሳየታቸው ምሥክርነት ለመስጠት መንገድ የከፈተላቸው እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
መዝሙር 45 እና ጸሎት