የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
ጥር አራተኛው ልዩ ዘመቻ መካሄድ የጀመረበት ወር ሲሆን በዚህ ወቅት ያደረግነው ከፍተኛ እንቅስቃሴ 7,099 የሚያህል አዲስ ከፍተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ቁጥር ላይ ለመድረስ አስችሎናል። ሥራችን ሕይወት አድን በመሆኑ ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማግኘት የምናደርገውን ጥረት መቀጠል ይኖርብናል። እንደ አውስትራሊያና ሰሜን አሜሪካ ያሉ ሩቅ ቦታዎችን ጨምሮ ከስምንት አገራት የተውጣጡ 48 ወንድሞችና እህቶች የአውሮፕላን ትኬት ዋጋ ከፍተኛ ቢሆንም የስብከት ሥራችንን ለመደገፍ ማመልከቻ ማስገባታቸውን ማየት እንዴት ያስደስታል! በአገራችን ያሉ በርካታ አስፋፊዎችና አቅኚዎች ከእነዚህ ወንድሞች ጋር ተመድበው ማገልገላቸው ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ‘ወደ መቄዶንያ ተሻግሮ’ መርዳት የሚያመጣውን ከፍተኛ እርካታ እንዲያጣጥሙ አድርጓቸዋል። (ሥራ 16:9) ታዲያ ወደ እነዚህ አካባቢዎች በመዛወር ረዘም ላለ ጊዜ ማገልገል ትችሉ እንደሆነና እንዳልሆነ ለምን አታስቡበትም?