ሰኔ 20 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሰኔ 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 31 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 13 አን. 31-39 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 45-51 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ መዝሙር 48:1 እስከ 49:9 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የአምላክ መንግሥት እውን የሆነ መስተዳድር ነው?—rs ገጽ 226 አን. 3 እስከ ገጽ 227 አን. 1 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ሕይወት ስጦታ ሆኖ ሳለ የራሳችንን መዳን ለመፈጸም ተግተን መሥራት የሚገባን ለምንድን ነው?—ሮም 6:23፤ ፊልጵ. 2:12 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ በሐምሌ ወር የምናበረክተው ጽሑፍ። በውይይት የሚቀርብ። በዚህ ወር ከሚበረከቱት ጽሑፎች መካከል መርጠህ ይዘታቸውን በአጭሩ ከልስ። ከዚያም አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ከሕፃናት አፍ። (ማቴ. 21:15, 16) በ2011 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ገጽ 53 አንቀጽ 3 እና ገጽ 58 ከአንቀጽ 1-2 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። በእያንዳንዱ ተሞክሮ ላይ ውይይት ካደረጋችሁ በኋላ ምን ትምህርት እንዳገኙ አድማጮችን ጠይቅ።
10 ደቂቃ፦ “በመንገድ ላይ ውጤታማ ምሥክርነት መስጠት” የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በጥያቄና መልስ የሚያቀርበው። ትምህርቱን ለክልላችሁ ሁኔታ እንዲስማማ አድርገህ አቅርበው። በትምህርቱ ውስጥ የቀረቡትን ነጥቦች በመጠቀም አንድ ወይም ሁለት አጠር ያሉ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
መዝሙር 16 እና ጸሎት