ሐምሌ 18 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሐምሌ 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 44 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 14 አን. 21-27 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 74-78 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ መዝሙር 77:1-20 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ዲያብሎስን መቃወም የምንችልባቸው መንገዶች—ያዕ. 4:7 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የአምላክ መንግሥት የይሖዋን ስም ያስቀድሳል—rs ገጽ 228 አን. 1-3 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። ዮሐንስ 4:3-24ን አንብብና ተወያዩበት። በአገልግሎታችን ኢየሱስን መምሰል የምንችለው እንዴት እንደሆነ ግለጽ። አንድ አስፋፊ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ሲመሰክር የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ፤ መቼቱ በተጨባጭ ሊፈጸም የሚችል ዓይነት ይሁን።
15 ደቂቃ፦ “ልጆቻችሁ ዝግጁ ናቸው?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። ክርስቲያኖች በትምህርት ቤት የሚያጋጥሟቸውን አንዳንድ ፈተናዎች ወላጆችም ሆነ ወጣቶች እንዲናገሩ አድርግ። በአንቀጽ 3 ላይ ከተወያያችሁ በኋላ አባትየው እንደ አስተማሪ ሆኖ ከልጁ ጋር ልምምድ ሲያደርግ የሚያሳይ አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ፤ ልጁ አጠያያቂ በሆነ የክፍል ሥራ ወይም እንቅስቃሴ ላይ ሊካፈል የማይችለው ለምን እንደሆነ ያስረዳል።
መዝሙር 51 እና ጸሎት