የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በሰማይ ያለውን አፍቃሪ አባታችንን ለማወደስ ከፍተኛ የአገልግሎት እንቅስቃሴ ያደረግንበት የሚያዝያ ወር በጣም አስደሳች ነበር! በዚህ ወር ትልልቅ ስብሰባዎች የተካሄዱ ቢሆንም በአገሪቱ ካሉት አስፋፊዎች መካከል 61 በመቶ የሚሆኑት አቅኚ ሆነው አገልግለዋል። ከእነዚህ መካከል 3,900 የሚሆኑት ረዳት አቅኚዎች የነበሩ ሲሆን ይህም ቀደም ሲል ከተመዘገበው ከፍተኛ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ከእጥፍ በላይ ነው። ብዙዎች ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ሌሎች ደግሞ ከረጅም ጊዜ በኋላ ረዳት አቅኚዎች ሆነው ማገልገል በመቻላቸው አመስጋኞች ሆነዋል። በዚህ ወር 9,128 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ያገኘን ከመሆኑም በተጨማሪ በአገልግሎት ሰዓት፣ በመጽሔትና በተመላልሶ መጠየቅ ረገድ አዲስ ከፍተኛ ቁጥር ተመዝግቧል። በመሆኑም በሚያዝያ ወር መጠነ ሰፊ ምሥክርነት የተሰጠ ሲሆን ፍላጎት ያሳዩትን በርካታ ሰዎች ተመልሰን ሄደን ‘ማጠጣት’ ይጠበቅብናል።