መስከረም 12 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 19 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 17 አን. 8-14 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 120-134 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ መዝሙር 124:1 እስከ 126:6 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የአምላክ መንግሥት ፍቅርና ስምምነት የሰፈነበት ዓለም እንዲፈጠር ያደርጋል—rs ገጽ 231 አን. 5-7 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ምንጊዜም ‘አጥርቶ የሚያይ ዓይን’ እንዲኖረን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?—ማቴ. 6:22, 23 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። በነሐሴ 2011 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 ላይ የሚገኘውን “የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች” የሚለውን ሣጥን ተወያዩበት። በሚያዝያ ወር እንዲህ ያለ አስደሳች ውጤት እንዲገኝ ላበረከተው አስተዋጽኦ ጉባኤውን አመስግን።
10 ደቂቃ፦ የሰዎችን ልብ መንካት የሚቻልበት መንገድ—ክፍል 1 በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 258 እስከ ገጽ 260 አንቀጽ 5 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በንግግር የሚቀርብ። የቀረቡትን ነጥቦች በመጠቀም አንድ ወይም ሁለት አጠር ያሉ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ የቱ እንደሚያፈራ አታውቁም። (መክ. 11:6) በ2011 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ገጽ 96 አንቀጽ 1-2 እንዲሁም ከገጽ 113 አንቀጽ 2 እስከ ገጽ 114 አንቀጽ 3 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። አድማጮች ምን ትምህርት እንዳገኙ ጠይቅ።
10 ደቂቃ፦ “የአገልግሎት መብታችሁን እንደ ውድ ሀብት አድርጋችሁ ተመልከቱት።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።
መዝሙር 22 እና ጸሎት