መስከረም 26 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 10 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 17 አን. 24-29 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 142-150 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ መዝሙር 144:1 እስከ 145:4 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የአምላክ መንግሥት በመጀመሪያው መቶ ዘመን መግዛት ጀምሯል?—rs ገጽ 232 አን. 4-6 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ “አድልዎ” ከማድረግ መቆጠብ የሚገባን ለምንድን ነው?—ያዕ. 2:1-4 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። “የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት የተባለውን ብሮሹር መጠቀም የሚቻልበት ሌላ መንገድ” የሚለውን ተወያዩበት። በገጽ 4 ላይ የሚገኘውን የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም ቅዳሜ፣ ጥቅምት 1 ላይ እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በዚህ ዕለት ሁሉም ተሳትፎ እንዲያደርጉ አበረታታ።
10 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። በውይይት የሚቀርብ። ከመጋቢት 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 4 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
15 ደቂቃ፦ በጥቅምት ወር መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። በውይይት የሚቀርብ። በአንድ ወይም በሁለት ደቂቃ ውስጥ በክልላችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉ አንዳንድ ርዕሶችን መርጠህ ተናገር። ከዚያም ሁለት ወይም ሦስት ርዕሶችን ምረጥና እያንዳንዱን ለማስተዋወቅ ምን ማለት እንደሚቻል ግለጽ። የሰዎችን የማወቅ ፍላጎት ለመቀስቀስ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዲሁም የትኞቹን ጥቅሶች ማንበብ እንደሚቻል እንዲናገሩ አድማጮችን በመጠየቅ ይህን ማድረግ ትችላለህ። የጥቅምት ንቁ! ልዩ እትም ስለሆነ ይህ መጽሔት ማንን ሊማርክ እንደሚችል እንዲሁም መጽሔቱን እንዴት በሰፊው ማሰራጨት እንደምንችል ሐሳብ እንዲሰጡ አድማጮችን ጋብዝ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 41 እና ጸሎት