ጥቅምት 17 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥቅምት 17 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 26 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 18 ከአን. 18-27 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ምሳሌ 12-16 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ምሳሌ 15:1-17 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ተቀባይነት ያለው ጸሎት በይሖዋ ዘንድ ጣፋጭ መዓዛ እንዳለው ዕጣን የሚታየው እንዴት ነው?—መዝ. 141:2፤ ራእይ 5:8 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የምንኖረው በመጨረሻዎቹ ቀኖች ውስጥ እንደሆነ የሚጠቁመው የትኛው ምልክት ነው?—rs ገጽ 234 አን. 1 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። በቅድሚያ ማቴዎስ 5:11, 12, 14-16, 23, 24ን አንብቡ። ከዚያም እነዚህ ጥቅሶች ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ እንዴት እንደሚረዱን ተወያዩበት።
10 ደቂቃ፦ ለምታነጋግሩት ሰው ጥቅሱን በቀጥታ ከመጽሐፍ ቅዱስ አሳዩት። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 145 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። አንድ አስፋፊ፣ በእጁ ባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ላይ የአምላክ ስም ለማይገኝ ፍላጎት ላሳየ ሰው ተመላልሶ መጠየቅ ሲያደርግ የሚያሳይ አጠር ያለ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ “ወደኋላ አትበሉ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። በጉባኤ ውስጥ ያሉ ልጆችም ሆኑ አዋቂዎች በትምህርት ቤት ሳሉ ምሥክርነት የሰጡባቸውን አጋጣሚዎች እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 19 እና ጸሎት