ጥቅምት 24 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥቅምት 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 28 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 1 ከአን. 1-7 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ምሳሌ 17-21 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ምሳሌ 17:21 እስከ 18:13 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ጦርነትና የምግብ እጥረት ‘የምልክቱ’ ክፍል የሆኑት እንዴት ነው?—rs ከገጽ 234 አን. 2 እስከ ገጽ 236 አን. 1 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ፈጣሪን ሳይሆን ፍጥረትን የሚያወድሱ ሰዎች ምን ዓይነት ሰዎች መሆናቸውን እያጋለጡ ነው?—ሮም 1:20 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። በኅዳር ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ከተናገርክ በኋላ አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
25 ደቂቃ፦ “ከይሖዋ የምትችለውን ያህል ትምህርት እየቀሰምክ ነው?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። በይሖዋ ድርጅት አማካኝነት ልዩ ሥልጠና ላገኘ አንድ አስፋፊ አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ።
መዝሙር 9 እና ጸሎት