የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ጥቅምት 31, 2011 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው።
1. ከይሖዋ ማሳሰቢያዎች ጋር መጣበቅ ያለብን ለምንድን ነው? (መዝ. 119:60, 61) [w00 12/1 ገጽ 14 አን. 3]
2. ከመዝሙር 133:1-3 ምን ትምህርት እናገኛለን? [w06 9/1 ገጽ 16 አን. 2]
3. ይሖዋ ዳዊትን ‘የመረመረው’ እና ‘መሄድ መተኛቱን ያወቀው’ በምን መንገድ ነው? (መዝ. 139:1, 3) [w06 9/1 ገጽ 16 አን. 5፤ w93 10/1 ገጽ 11 አን. 6]
4. ይሖዋ አገልጋዮቹን ‘የሚደግፈው’ ወይም ‘የሚያነሳው’ ምን ዓይነት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሟቸው ነው? (መዝ. 145:14) [w04 1/15 ገጽ 17 አን. 11]
5. በምሳሌ 6:12-14 (የ1954 ትርጉም) ላይ የተጠቀሰው ሰው እንደ ምናምንቴ እንዲቆጠር ያደረገው ምንድን ነው? [w00 9/15 ከገጽ 26 አን. 6 እስከ ገጽ 27 አን. 1]
6. ጠቢብ ሰው ‘ትእዛዝ የሚቀበለው’ ለምንድን ነው? (ምሳሌ 10:8) [w01 7/15 ገጽ 26 አን. 1]
7. ጥበበኛ ሰው ዘለፋ ወይም መሠረተ ቢስ ትችት ሲሰነዘርበት ምላሽ የሚሰጥበት መንገድ ከሞኝ ሰው የሚለየው እንዴት ነው? (ምሳሌ 12:16) [w03 3/15 ገጽ 27 አን. 4-5]
8. አዎንታዊ አመለካከት መያዝ “የማይቋረጥ” ደስታ እንዲኖረን የሚያደረገው እንዴት ነው? (ምሳሌ 15:15) [w06 7/1 ገጽ 16 አን. 6]
9. ‘ጥበበኛ ልብ ማግኘት’ ምን ነገሮችን ያጠቃልላል? እንዲህ የሚያደርግ ሰው “የገዛ ነፍሱን ይወዳል” ሊባል የሚችለውስ እንዴት ነው? (ምሳሌ 19:8 NW) [w99 7/1 ገጽ 18 አን. 4፤ it-1-E ገጽ 1059 አን. 1]
10. ማስተዋል ቤተሰብን የሚጠቅመው እንዴት ነው? (ምሳሌ 24:3) [w06 9/15 ገጽ 27 አን. 11፤ be ገጽ 31 አን. 6]