ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ጥቅምት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ፍላጎት ያለው ሰው ስታገኙ እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለውን ትራክት አበርክቱለት፤ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ኅዳር፦ መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው? ከዚህ ብሮሹር ጋር ወይም ደግሞ በዚህ ብሮሹር ፋንታ በሐምሌና በነሐሴ 2011 ያበረከትነውን ማንኛውንም ባለ 32 ገጽ ብሮሹር መጠቀም ይቻላል። ታኅሣሥ፦ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው። የቤቱ ባለቤት ልጆች ካሉት ከታላቁ አስተማሪ ተማር ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ የተባሉትን መጽሐፎች አበርክቱ። ጥር፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ሰዎችን በምታነጋግሩበት በመጀመሪያው ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ።
◼ ጊዜያዊ ልዩ አቅኚዎች፦ ከጥር እስከ መጋቢት ባሉት ወራት አዳዲስ ክልሎችን ለመሸፈን በሚደረገው ዘመቻ ጊዜያዊ ልዩ አቅኚ ሆናችሁ ማገልገል የምትፈልጉ የዘወትር አቅኚዎች፣ ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች የሚከተሉትን መረጃዎች ጽፋችሁ በጉባኤያችሁ የአገልግሎት ኮሚቴ በኩል እንድትልኩ ትጠየቃላችሁ። እባካችሁ እነዚህን መረጃዎች አካትቱ፦ 1) ስም፣ 2) የትውልድ ዘመን፣ 3) የጥምቀት ቀን፣ 4) የጉባኤው ስም፣ 5) የጋብቻ ሁኔታ፣ 6) በሥራችሁ የሚተዳደሩ ሰዎች ካሉ ጥቀሱ፣ 7) የምትናገሯቸው ቋንቋዎች፣ 8) ዘመቻው ሲያበቃ በልዩ አቅኚነት መቀጠል የምትፈልጉ ከሆነ ግለጹ። ከዚያም የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ የአመልካቹን ብቃት በተመለከተ ሐሳብ ካሰፈረ በኋላ ደብዳቤው እስከ ጥቅምት 31 ቀን 2011 ባለው ጊዜ ውስጥ ለቅርንጫፍ ቢሮው እንዲደርስ ቢያደርግ ጥሩ ነው። የሚያስፈልጉት ቀናተኛ ሰባኪዎች እንዲሁም ትጉህና ውጤታማ ሠራተኞች ናቸው። ከቤት ወደ ቤት በመሄድ ክልል የሚሸፍን ቀናተኛ ሰባኪ ነው? ተመላልሶ መጠየቅ በማድረግ ረገድ ቁም ነገረኛ ነው? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን በመምራት ረገድ ጥሩ አስተማሪ ነው? ከሌሎች ጋር በሰላም ለመሥራት ጥረት በማድረግ የመንፈስ ፍሬ እያፈራ ነው? ግለሰቡ ለዚህ ቅዱስ የአገልግሎት መብት ይበቃል ትላላችሁ? አመልካቹ ብቁ አይደለም ብላችሁ ከወሰናችሁ ማመልከቻውን ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው መላክ አያስፈልግም። ከዚህ ይልቅ ውሳኔያችሁን ከነገራችሁት በኋላ ማሻሻያ እንዲያደርግ በደግነት ምክር ስጡት። ውሳኔ ላይ ስንደርስ ብቁ ሆነው ያገኘናቸውን ወንድሞችና እህቶች በጉባኤያቸው በኩል እናሳውቃቸዋለን።
◼ እንደገና የደረሱን ጽሑፎች፦ አማርኛ፦ የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፤ እንግሊዝኛ፦ ባለማጣቀሻው የአዲስ ዓለም ትርጉም (Rbi-8)፣ ጋይዳንስ ኦቭ ጎድ፣ T-24 (ኢየሱስ ክርስቶስ—ማን ነው?)፤ ኦሮምኛ፦ እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ?፣ የቤተሰብ ደስታ፤ ትግርኛ፦ T-22 (ዓለምን የሚገዛው ማን ነው?)