ታኅሣሥ 12 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ታኅሣሥ 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 43 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 3 ከአን. 1-10 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢሳይያስ 6-10 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ኢሳይያስ 6:1-13 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ አምላክ ክፉዎችን ሳያጠፋ ይህን ያህል ጊዜ የቆየው ለምንድን ነው?—rs ገጽ 240 ከአን. 5-7 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ፍቅር ፈጽሞ የማይከስመው ለምንድን ነው?—1 ቆሮ. 13:8፤ 1 ዮሐ. 4:8 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ የ2012 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት። በትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር። ከ2012 ፕሮግራም ላይ ለጉባኤው የሚያስፈልጉ አንዳንድ ነጥቦችን ጥቀስ። ረዳት ምክር ሰጪው ያለውን ኃላፊነት ተናገር። ሁሉም ክፍል ሲሰጣቸው ተገኝተው በማቅረብ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጎላ ያሉ ነጥቦች ላይ ሐሳብ በመስጠት እንዲሁም ከአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ላይ በየሳምንቱ የሚሰጡትን ሐሳቦች ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ትጉዎች እንዲሆኑ አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ “ከስብከቱ ሥራችን የምናርፍበት ጊዜ የለም!” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። በአንቀጽ 2 ላይ ስትወያዩ መደበኛ ባልሆነ መንገድ በመስበክ ውጤታማ ለሆነ አንድ አስፋፊ ቃለ ምልልስ አድርግ። ዝግጅት የሚያደርገው እንዴት እንደሆነ ጠይቀው፤ እንዲሁም አንድ ግሩም ተሞክሮ እንዲናገር ጋብዘው።
መዝሙር 24 እና ጸሎት