ታኅሣሥ 19 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ታኅሣሥ 19 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 43 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 3 ከአን. 11-19 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢሳይያስ 11-16 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ኢሳይያስ 13:1-16 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ በማየት ሳይሆን በእምነት የምንመላለሰው ለምንድን ነው?—2 ቆሮ. 5:7 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ፦ “ዛሬ ያሉት ሁኔታዎች ከቀድሞው የተለዩ አይደሉም። ጦርነት፣ ረሀብ፣ የመሬት መንቀጥቀጥና ወንጀል ጠፍቶ አያውቅም”—rs ገጽ 241 አን. 2 እስከ ገጽ 242 አን. 1 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። በጥር ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ከተናገርክ በኋላ አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ በአስቸጋሪ ወቅትም አገልግሉ። (2 ጢሞ. 4:2) በ2011 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ከገጽ 121 እስከ ገጽ 122 አንቀጽ 4 እና በገጽ 226 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ምን ትምህርት እንዳገኙ አድማጮችን ጠይቅ።
10 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በውይይት የሚያቀርበው።
መዝሙር 47 እና ጸሎት