መጋቢት 26 የሚጀምር ሳምንት
መጋቢት 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 47 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 7 ከአን. 24-27 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 12-16 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ኤርምያስ 13:1-14 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ከጌታ ራት መካፈል ያለባቸው እነማን ናቸው?—rs ገጽ 267 አን. 2, 3 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የመታሰቢያው በዓል መከበር የሚኖርበት በየስንት ጊዜው ነው? የሚከበረውስ መቼ ነው?—rs ገጽ 268 አን. 2, 3 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። ጉባኤው የመታሰቢያው በዓል የመጋበዣ ወረቀት ያልተሰራጨባቸው ስንት ክልሎች እንደቀሩት ተናገር።
10 ደቂቃ፦ እንግዳ ተቀባይ መሆንን አትርሱ። (ዕብ. 13:1, 2) በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ጉባኤው ለመታሰቢያው በዓል ያደረጋቸውን ዝግጅቶች ተናገር። በበዓሉ ላይ ለሚገኙ እንግዶችም ሆነ ለቀዘቀዙ አስፋፊዎች የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ ማሳየት የምንችልባቸውን አንዳንድ መንገዶች ጥቀስ። ሁለት ክፍሎች ያሉት አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። የመጀመሪያው ክፍል አንድ አስፋፊ መጋበዣ ወረቀት ደርሶት ለመጣ ሰው ከፕሮግራሙ በፊት ጥሩ አቀባበል ሲያደርግለት የሚያሳይ ነው። ሁለተኛው ደግሞ አስፋፊው፣ ከፕሮግራሙ በኋላ የግለሰቡን ፍላጎት ይበልጥ ለማነሳሳት የሚያስችል ጥረት ለማድረግ ቀጠሮ ሲይዝ የሚያሳይ ነው።
20 ደቂቃ፦ “አስደናቂ የፍጥረት ሥራዎች የአምላክን ክብር ይገልጣሉ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። በመጀመሪያውና በመጨረሻው አንቀጾች ውስጥ ያሉትን ሐሳቦች መግቢያና መደምደሚያ አድርገህ ተጠቀምባቸው። ይህን ፊልም በማየታቸው የተጠቀሙት እንዴት እንደሆነ ሐሳብ እንዲሰጡ አድማጮችን ጋብዝ። ፊልሙን በአገልግሎታችን መጠቀም የምንችለው እንዴት እንደሆነ ተወያዩ።
መዝሙር 15 እና ጸሎት