የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በዚህ አገር የተደረጉት የአውራጃ ስብሰባዎች ከተጠናቀቁ በኋላ በኅዳር ወር ባደረግነው የአገልግሎት እንቅስቃሴ 9,236 የደረሰ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ተመዝግቧል፤ እንዲሁም በዚህ ወር 259,226 መጽሔቶች የተበረከቱ ሲሆን ይህ አኃዝ ከዚህ በፊት ከተመዘገቡት ሁሉ ከፍተኛው ነው። በዚህ ወር 7,160 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ተመርተዋል። አዲስ ባገኘናቸው ብሮሹሮች ታግዘን በመጪዎቹ ወራትም ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን እንደምናስጀምር ተስፋ እናደርጋለን።