ሚያዝያ 9 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሚያዝያ 9 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 42 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 8 ከአን. 8-13 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 22-24 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ኤርምያስ 23:15-23 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ በአዲሱ ዓለም ውስጥ መኖር ፈጽሞ አሰልቺ የማይሆነው ለምንድን ነው? (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር በሥራ ላይ ማዋል ትዳር እንዲጠናከር ያደርጋል—rs ገጽ 253 ከአን. 5-8 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ የ2012 የዓመት መጽሐፍን በጥሩ ሁኔታ ተጠቀሙበት። በመጀመሪያ “ከበላይ አካል የተላከ ደብዳቤ” የሚለውን በንግግር አቅርብ። ከዚያም አድማጮች “ያለፈው ዓመት ጎላ ያሉ እንቅስቃሴዎች” ከሚለው ክፍል ላይ አበረታች ሆኖ ያገኙትን ሐሳብ ወይም ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ። በተጨማሪም በየካቲት የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ከወጣው ዓለም አቀፍ ሪፖርት ላይ ያስደነቃቸውን ነገር እንዲናገሩ ጋብዝ። ሁሉም የዓመት መጽሐፉን ከዳር እስከ ዳር እንዲያነቡ በማበረታታት ክፍሉን ደምድም።
15 ደቂቃ፦ “የማስተማር ችሎታን ለማሻሻል የሚረዱ ሦስት ነጥቦች።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አንቀጽ 2 ላይ ስትወያዩ አንድ አስፋፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ ገጽ 3 ላይ ባለው የመጀመሪያ አንቀጽ ተጠቅሞ የቤቱን ባለቤት ሲያነጋግር የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። አስፋፊው የኢዮብ 10:15ን ጥቅስ ለቤቱ ባለቤት ከመጽሐፉ ላይ ካነበበለት በኋላ አንድ ወይም ሁለት ደቂቃ ወስዶ ስለ ኢዮብ ማንነት ማብራሪያ ይሰጠዋል። ከዚያም አስፋፊው ስለ ኢዮብ የሰጠው ማብራሪያ ትክክል ቢሆንም ጥሩ የማስተማር ዘዴ ያልሆነበትን ምክንያት አድማጮችን ጠይቅ።
መዝሙር 10 እና ጸሎት