የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በታኅሣሥ ወር መጨረሻ ላይ በአስፋፊዎች (9,250) እና በዘወትር አቅኚዎች (1,592) ረገድ ከምንጊዜውም የበለጠ ከፍተኛ ቁጥር አግኝተናል። በአሁኑ ጊዜ ከአምስት አስፋፊዎች መካከል አንዱ የዘወትር አቅኚ ወይም ልዩ አቅኚ መሆኑን ማወቃችን ያስደስተናል። በተጨማሪም ብዙዎቻችሁ በመጋቢት ወር ረዳት አቅኚ ሆናችሁ በማገልገል ደስታ እንዳገኛችሁ ምንም ጥርጥር የለውም። በዚህ መንገድ ለይሖዋ ክብር የሚያመጣ የመንግሥት ፍሬ ማፍራት ችለናል። ወደፊት ደግሞ ክልሎችን ለመሸፈን የሚደረገው ዘመቻና ከመታሰቢያው በዓል ጋር በተያያዘ የሚደረገው እንቅስቃሴ የሚያስገኘውን ውጤት ለመስማት እንጓጓለን። ትጋት የታከለበት ጥረት ስታደርጉ የምታገኟቸውን ፍላጎት ያላቸው ሰዎች በሚገባ ተከታትላችሁ እንድትረዱ እናበረታታችኋለን።