ግንቦት 28 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ግንቦት 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 49 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 10 ከአን. 1-9 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 49-50 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ኤርምያስ 49:28-39 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የይሖዋ ስም “ጽኑ ግንብ” የሆነው እንዴት ነው?—ምሳሌ 18:10 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ማርያም ከነሥጋዊ አካሏ ወደ ሰማይ አርጋለች?—rs ከገጽ 257 አን. 3 እስከ ገጽ 258 አን. 1 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። በቅርብ ለደረሰው የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የተዘጋጀውን የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም በሰኔ ወር የመጀመሪያው ቅዳሜ እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
25 ደቂቃ፦ “የይሖዋ ምሥክሮች ያሳዩት በተግባር የተደገፈ እምነት፣ ክፍል 2፦ ብርሃኑ ይብራ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። በመጀመሪያውና በመጨረሻው አንቀጾች ውስጥ ያሉትን ሐሳቦች መግቢያና መደምደሚያ አድርገህ ተጠቀምባቸው።
መዝሙር 45 እና ጸሎት