ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ግንቦት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ፍላጎት ያለው ሰው ስታገኙ እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለውን ትራክት አበርክቱለት፤ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ሰኔ፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ሰዎችን በምታነጋግሩበት በመጀመሪያው ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ሐምሌ እና ነሐሴ፦ ብሮሹሮች። ሕይወት የተገኘው በፍጥረት ነው?፣ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ነቅተህ ጠብቅ!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?፣ ሪል ፌይዝ—ዩር ኪ ቱ ኤ ሃፒ ላይፍ (ለሙስሊሞች) እና ዘ ሮድ ቱ ኤቨርላስቲንግ ላይፍ—ሃቭ ዩ ፋውንድ ኢት?፣ ፓዝዌይ ቱ ፒስ ኤንድ ሃፒነስ (ለቡዲስቶች)፣ ኤ ሳቲስፋይንግ ላይፍ—ሃው ቱ አቴይን ኢት (እውን አካል ያለው ፈጣሪ እንዲሁም በመለኮት መሪነት የተጻፈ መጽሐፍ ስለመኖሩ ምንም የማያውቁ ሰዎችን ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ)፣ ላስቲንግ ፒስ ኤንድ ሃፒነስ—ሃው ቱ ፋይንድ ዘም (ለቻይናውያን)። ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አሊያም ደግሞ የግለሰቡን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ ከተባሉት ብሮሹሮች መካከል አንዱን በማበርከት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ።