ሰኔ 4 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሰኔ 4 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 45 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 10 ከአን. 10-18 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 51-52 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ኤርምያስ 52:17-27 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ማርያምን እንደ አማላጅ በመቁጠር ለእሷ ጸሎት ማቅረብ ተገቢ ነው?—rs ገጽ 258 ከአን. 2-4 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የሰው ልጆች በይሖዋ “ሚስጥራዊ ቦታ” መኖር የሚችሉት እንዴት ነው?—መዝ. 91:1, 2, 9 NW (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ የሰዎችን ልብ መንካት የሚቻልበት መንገድ—ክፍል 2 በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 261 አንቀጽ 1 እስከ ገጽ 262 መጨረሻ ድረስ ባሉት ሐሳቦች ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ በሰኔ ወር መጽሔቶችን ለማበርከት የሚረዱ ሐሳቦች። በውይይት የሚቀርብ። በአንድ ወይም በሁለት ደቂቃ ውስጥ በክልላችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉ አንዳንድ ርዕሶችን መርጠህ ተናገር። ከዚያም በመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የሽፋን ርዕስ ዙሪያ የሰዎችን የማወቅ ፍላጎት ለመቀስቀስ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዲሁም የትኞቹን ጥቅሶች ማንበብ እንደሚቻል እንዲናገሩ አድማጮችን ጠይቅ። በንቁ! መጽሔት የሽፋን ርዕስ ዙሪያም ተመሳሳይ ጥያቄዎች አቅርብ፤ ጊዜ ካለህ ከመጠበቂያ ግንብ ወይም ከንቁ! መጽሔት አንድ ተጨማሪ ርዕስ ማከል ትችላለህ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 29 እና ጸሎት