የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
የካቲት አጭር ወር ቢሆንም እናንተ ያደረጋችሁት ትጋት የተሞላበት እንቅስቃሴ ልዩ ወር እንዲሆን አድርጎታል። በድምሩ 409 የአገራችን አስፋፊዎችና ከውጭ አገር የመጡ 16 ወንድሞችና እህቶች በዘንድሮው የመቄዶንያ ዘመቻ ላይ ተካፍለዋል። በዚህ ወር 9,305 አስፋፊዎች፣ 1,639 የዘወትር አቅኚዎች እንዲሁም 7,593 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች የነበሩ ሲሆን ይህ ሁሉ አዲስ ከፍተኛ ቁጥር ነው። በመጽሔት ስርጭትም ቢሆን አዲስ ከፍተኛ ቁጥር የተገኘ ሲሆን ባለፈው ዓመት ከተበረከተው 37 በመቶ ብልጫ ነበረው! ሌላው አስደሳች ነገር ደግሞ በየጉባኤው ያሉት አስፋፊዎች ተመላልሶ በመጠየቅ ረገድ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ነው። የዚህ ወር ጠቅላላ የተመላልሶ መጠየቅ ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 19 በመቶ ይበልጣል! በሌላ አነጋገር እያንዳንዱ አስፋፊ በአማካይ 5.7 ተመላልሶ መጠየቅ አድርጓል። ይህ በእርግጥ የሚያስመሰግን ነው! በመታሰቢያው በዓል ሰሞን ያደረግነው ልዩ የአገልግሎት እንቅስቃሴ ምን ውጤት እንዳስገኘ ለመስማት በጉጉት እንጠባበቃለን።