ማስታወቂያዎች
◼የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ሰኔ፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ሰዎችን በምታነጋግሩበት በመጀመሪያው ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ሐምሌ እና ነሐሴ፦ ብሮሹሮች። መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው? እና የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ! ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አሊያም ደግሞ የግለሰቡን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ ከተባሉት ብሮሹሮች መካከል አንዱን በማበርከት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። መስከረም፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አሊያም ደግሞ የግለሰቡን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ ከተባሉት ብሮሹሮች መካከል አንዱን በማበርከት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ።
◼በቅርቡ በምናደርገው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ አወር ሆል አሶሲየሽን ኦቭ ብራዘርስ (መላው የወንድማማች ማኅበር) የተሰኘውን ፊልም እንከልሳለን። ፊልሙን ማግኘት የምትፈልጉ ከሆነ በተቻለ ፍጥነት በጉባኤው በኩል ማዘዝ ይኖርባችኋል።
◼አዳዲስ ጽሑፎች፦ አማርኛ፦ የይሖዋ ምሥክሮች—እነማን ናቸው? ምን ብለው ያምናሉ? (ባለ 32 ገጽ ብሮሹር)፤ ሲዳምኛ፦ ዘ ሮድ ቱ ኤቨርላስቲንግ ላይፍ—ሃቭ ዩ ፋውንድ ኢት?
◼ጉባኤዎች ዓመታዊ የጽሑፍ ትእዛዛቸውን እጅግ ቢዘገይ እስከ ሐምሌ 1, 2012 ድረስ ወደ ቅርንጫፍ ቢሯችን መላክ ይኖርባቸዋል። ከዓመታዊ ጽሑፎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ የ2013 ቀን መቁጠሪያ፣ ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር 2013፣ የ2013 የዓመት መጽሐፍ፣ የ2012 የንቁ! እና የመጠበቂያ ግንብ ጥራዞች፣ የ2012 ዎችታወር ላይብራሪ፣ ዓመታዊ የጽሑፎች ማውጫ።