ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ሐምሌ እና ነሐሴ፦ ብሮሹሮች። መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው? እና የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ! መስከረም እና ጥቅምት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አሊያም ደግሞ የግለሰቡን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ ከተባሉት ብሮሹሮች መካከል አንዱን በማበርከት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ።
◼ ከነሐሴ 1 ጀምሮ ለይሖዋ ዘምሩ—በድምፅ የተቀነባበረ፣ ዲስክ 5 jw.org በተባለው ድረ ገጽ ላይ ስለሚወጣ ከዚያ ቀን ጀምሮ መዝሙሮቹን ዳውንሎድ ማደረግ ይቻላል። መዝሙሮቹ መጀመሪያ በድረ ገጻችን ላይ የሚለቀቀው በእንግሊዝኛ ሲሆን ከጊዜ በኋላ በሌሎች ቋንቋዎችም ይለቀቃል። መዝሙሮቹን በሲዲ ማግኘት ከፈለጋችሁ በጉባኤያችሁ በኩል ማዘዝ ትችላላችሁ። ይሁንና ፋይሎችን ከድረ ገጻችን ላይ ዳውንሎድ ማድረግ በሲዲ ቀርጾ ከመላክ ጋር ሲነጻጸር ወጪው ዝቅ ያለ በመሆኑ የምትችሉ ሁሉ መዝሙሮቹን ዳውንሎድ እንድታደርጉ እናበረታታችኋለን። የመጀመሪያዎቹ አራት ዲስኮችም በድረ ገጹ ላይ እንደሚገኙ በዚህ አጋጣሚ ልናስታውሳችሁ እንወዳለን።
◼ አዳዲስ ጽሑፎች፦ እንግሊዝኛ፦ የ2012 የዓመት መጽሐፍ በሲዲ፤ ሲዳምኛ፦ አፕላይ ዩርሰልፍ ቱ ሪዲንግ ኤንድ ራይቲንግ።
◼ ከ2013 ጀምሮ የቀን መቁጠሪያ በአማርኛ ቋንቋም ይዘጋጃል። እባካችሁ ትእዛዛችሁን እስከ ሐምሌ 1, 2012 ድረስ ላኩ።
◼ ዓመታዊ ጽሑፎች እጅግ ቢዘገይ እስከ ሐምሌ 1, 2012 ቅርንጫፍ ቢሯችን መድረስ እንዲችሉ ጉባኤዎች ትእዛዛቸውን አሁኑኑ መላክ ይኖርባቸዋል። ከዓመታዊ ጽሑፎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ የ2013 የቀን መቁጠሪያ፣ ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር 2013፣ የ2013 የዓመት መጽሐፍ፣ የ2012 የንቁ! እና የመጠበቂያ ግንብ ጥራዞች፣ የ2012 ዋችታወር ላይብረሪ፣ ዓመታዊ የጽሑፎች ማውጫ። እነዚህን ጽሑፎች በእንግሊዝኛ ብቻ ሳይሆን በፈረንሳይኛ፣ በጀርመንኛ፣ በጣሊያንኛ፣ በስፓንኛ፣ በፖርቱጋልኛ፣ በሩሲያኛ፣ በስዋሂሊ (ከጥራዞቹ በስተቀር) እና በሌሎች ቋንቋዎች ማግኘት ይቻላል። ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር 2013 ደግሞ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በትግርኛ፣ በኪንያርዋንዳና በቻይንኛ ይገኛል። በተጨማሪም በትላልቅ ፊደላት የተዘጋጀውን እትም በእንግሊዝኛ ማግኘት ይቻላል።