የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/12 ገጽ 8
  • ነሐሴ 6 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ነሐሴ 6 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ነሐሴ 6 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
km 7/12 ገጽ 8

ነሐሴ 6 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም

ነሐሴ 6 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 23 እና ጸሎት

□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦

fy ምዕ. 13 ከአን. 1-9 (25 ደቂቃ)

□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦

የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 24-27 (10 ደቂቃ)

ቁ. 1፦ ሕዝቅኤል 24:15-27 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)

ቁ. 2፦ አምላክ እስራኤላውያን ጦርነት እንዲያደርጉ የፈቀደላቸው ለምንድን ነው?​—rs ከገጽ 271 አን. 3 እስከ ገጽ 272 አን. 3 (5 ደቂቃ)

ቁ. 3፦ ሕዝቅኤል 18:20 ከ⁠ዘፀአት 20:5 ጋር ይጋጫል? (5 ደቂቃ)

□ የአገልግሎት ስብሰባ፦

መዝሙር 41

5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።

10 ደቂቃ፦ ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ተዘጋጅታችኋል? በውይይት የሚቀርብ። ክርስቲያን ወጣቶች በትምህርት ቤት የሚያጋጥሟቸውን አንዳንድ ተፈታታኝ ሁኔታዎች እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ። ወላጆች ልጆቻቸው በትምህርት ቤት የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች መቋቋምና ስለ እምነታቸው ማስረዳት እንዲችሉ ከወዲሁ ለማዘጋጀት በቤተሰብ አምልኮ ወቅት የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫን፣ የወጣቶች ጥያቄ የተባሉትን መጻሕፍትና ሌሎች ቲኦክራሲያዊ መሣሪያዎችን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ግለጽ። (1 ጴጥ. 3:15) ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ወይም ሁለት ርዕሰ ጉዳዮች ምረጥና በዚያ ዙሪያ ከጽሑፎቻችን ያገኘሃቸውን አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦች ተናገር። ተማሪዎች በነበሩበት ወቅት በትምህርት ቤት ውስጥ ምሥክርነቱን መስጠት የቻሉት እንዴት እንደነበር እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።

10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

10 ደቂቃ፦ በነሐሴ ወር መጽሔቶችን ለማበርከት የሚረዱ ሐሳቦች። በውይይት የሚቀርብ። መጽሔቶቹ በክልላችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉበትን ምክንያት ከ30 እስከ 60 ሴኮንድ ባለው ጊዜ ውስጥ ተናገር። ከዚያም በመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የሽፋን ርዕስ ዙሪያ የሰዎችን የማወቅ ፍላጎት ለመቀስቀስ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዲሁም የትኞቹን ጥቅሶች ማንበብ እንዳሰቡ አድማጮችን ጠይቅ። በንቁ! መጽሔት የሽፋን ርዕስ ዙሪያም ተመሳሳይ ጥያቄዎችን አቅርብ፤ ጊዜ ካለህ ከመጠበቂያ ግንብ ወይም ከንቁ! መጽሔት አንድ ተጨማሪ ርዕስ ማከል ትችላለህ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

መዝሙር 17 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ