ነሐሴ 13 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ነሐሴ 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 18 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 13 ከአን. 10-16 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 28-31 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ሕዝቅኤል 28:17-26 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ኢየሱስ ክርስቶስን በተመለከተ የተሳሳቱ ትምህርቶችን ከእውነቱ መለየት (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ክርስቲያኖች በፖለቲካ ጉዳዮች ከመካፈል ጋር በተያያዘ የሚመሩባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የትኞቹ ናቸው?—(rs ከገጽ 272 አን. 4 እስከ ገጽ 273 አን. 3 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ ለተመላልሶ መጠየቅ መሠረት መጣል። በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ፦ (1) የቤቱን ባለቤት በምናነጋግርበት በመጀመሪያው ቀን ላይ ለተመላልሶ መጠየቅ መሠረት መጣላችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? እንዲህ ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው? (2) በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት ልንወያይበት የምንችል የቤቱን ባለቤት ትኩረት የሚስብ ጥያቄ መምረጥ የምንችለው እንዴት ነው? (3) ቀጣዩን ውይይት የምናደርግበትን ቁርጥ ያለ ቀጠሮ መያዛችን የሚቻል ከሆነም የግለሰቡን ስልክ ቁጥር ወይም የኢ-ሜይል አድራሻ መውሰዳችን ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው? (4) ሳንዘገይ ምናልባትም በጥቂት ቀናት ውስጥ ተመልሰን መሄድ ያለብን ለምንድን ነው? (5) የቤቱን ባለቤት ባነጋገርንበት በመጀመሪያው ቀን ላይ የትኞቹን መረጃዎች መጻፍ ይኖርብናል?
10 ደቂቃ፦ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ለሚገኙ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ። በዚህ አገልግሎት እንዲካፈሉ ያነሳሳቸው ምንድን ነው? በሙሉ ጊዜ አገልግሎት እንዳይቀጥሉ እንቅፋት የሚሆኑባቸው ምን ነገሮች አጋጥመዋቸዋል? በዚህ አገልግሎት እንዲቀጥሉ የረዳቸው ምንድን ነው? ምን በረከቶችን አግኝተዋል? አስፋፊዎች፣ በቀጣዩ የአገልግሎት ዓመት የዘወትር አቅኚ ለመሆን በቁም ነገር እንዲያስቡ አበረታታቸው።
10 ደቂቃ፦ “ሕሊናህን ጠብቅ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። ልዩ ስብሰባው የሚካሄድበት ቀን የሚታወቅ ከሆነ ተናገር።
መዝሙር 32 እና ጸሎት