ነሐሴ 20 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ነሐሴ 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 52 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 13 ከአን. 17-22 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 32-34 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ሕዝቅኤል 34:15-28 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ክርስቲያኖች ከብሔራዊ ስሜት ጋር የተያያዙ ሥነ ሥርዓቶች ላይ በመካፈል ረገድ የሚመሩባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የትኞቹ ናቸው?—rs ከገጽ 273 አን. 4 እስከ ገጽ 275 አን. 1 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ትርጉም ያለው ጸሎት ቃላትን ከመደርደር የበለጠ ነገር ይጨምራል የምንለው ለምንድን ነው?—መዝ. 145:18፤ ማቴ. 22:37 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ፦ ‘የማምነው በዝግመተ ለውጥ ነው።’ በማመራመር መጽሐፍ ከገጽ 127 እስከ ገጽ 129 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ‘አምላክ ሰውን የፈጠረው በዝግመተ ለውጥ አማካኝነት ነው ብዬ አምናለሁ’ ለሚል ሰው ምን ዓይነት መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ አጠር ያለ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ እርስ በርስ እንበረታታ። (ዕብ. 10:25) በ2012 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ገጽ 108 አንቀጽ 2፣ ገጽ 109 አንቀጽ 2 እንዲሁም ገጽ 181 አንቀጽ 1 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ምን ትምህርት እንዳገኙ አድማጮችን ጠይቅ።
10 ደቂቃ፦ “አእምሮህን ጠብቅ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። የወረዳ ስብሰባው የሚካሄድበት ቀን የሚታወቅ ከሆነ ተናገር።
መዝሙር 42 እና ጸሎት