ኅዳር 26 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ኅዳር 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 31 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
w09 5/15 ከገጽ 10 አን. 7 እስከ ገጽ 11 አን. 13 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሚክያስ 1-7 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ሚክያስ 3:1-12 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ በሉቃስ 23:43 ላይ የተጠቀሰው ገነት ምድራዊ መሆኑን የሚያመለክተን ምንድን ነው?—rs ከገጽ 287 አን. 2 እስከ ገጽ 288 አን. 2 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ይሖዋ ጸሎት ሰሚ አምላክ ነው እንድንል የሚያደርገን ምንድን ነው?—1 ዮሐ. 5:14 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ በመጀመሪያው ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር። በቅርብ ጊዜ ለደረሰን መጠበቂያ ግንብ የተዘጋጀውን የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም በታኅሣሥ ወር የመጀመሪያ ቅዳሜ እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሁሉም ጥናት ለማስጀመር ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ።
10 ደቂቃ፦ የእነሱ ትርፍ የሌሎችን ጉድለት ሸፈነ። በኅዳር 15, 2012 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 8-9 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
15 ደቂቃ፦ “ወደ ኋላ አትበሉ—ፕሮግራማችን የተጣበበ ቢሆንም ሁኔታችንን ማመቻቸት።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። የተጣበበ ፕሮግራም ቢኖረውም ጥናቶች ለሚመራ አንድ አስፋፊ አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ።
መዝሙር 25 እና ጸሎት