ታኅሣሥ 3 የሚጀምር ሳምንት
ታኅሣሥ 3 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 32 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
w09 5/15 ከገጽ 12 አን. 14 እስከ ገጽ 13 አን. 19 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ናሆም 1 እስከ ዕንባቆም 3 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዕንባቆም 2:1-14 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ስለ እውነት በልበ ሙሉነት መናገር የምንችለው እንዴት ነው?—2 ጢሞ. 1:7, 8 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ማናችንም ብንሆን እውነተኛ እውቀትና ጥበብ ልናገኝ የምንችለው እንዴት ነው?—rs ከገጽ 288 አን. 3 እስከ ገጽ 289 አን. 2 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በታኅሣሥ ወር መጽሔቶችን ለማበርከት የሚረዱ ሐሳቦች። በውይይት የሚቀርብ። መጽሔቶቹ በክልላችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉበትን ምክንያት ከ30 እስከ 60 ሴኮንድ ባለው ጊዜ ውስጥ ተናገር። ከዚያም በመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የሽፋን ርዕስ ዙሪያ የሰዎችን የማወቅ ፍላጎት ለመቀስቀስ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዲሁም የትኞቹን ጥቅሶች ማንበብ እንዳሰቡ አድማጮችን ጠይቅ። በንቁ! መጽሔት የሽፋን ርዕስ ዙሪያም ተመሳሳይ ጥያቄዎችን አቅርብ፤ ጊዜ ካለህ ከመጠበቂያ ግንብ ወይም ከንቁ! መጽሔት አንድ ተጨማሪ ርዕስ ማከል ትችላለህ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ ትራክቶችን በማበርከት የተገኙ ተሞክሮዎች። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በውይይት የሚያቀርበው። አድማጮች በኅዳር ወር ትራክቶችን ሲያበረክቱ ያገኙትን ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ። በዚህ ረገድ የተሳካላቸው ሁለት አስፋፊዎች ትራክቶችን ከቤት ወደ ቤት ማበርከት የቻሉት እንዴት እንደሆነ በሠርቶ ማሳያ መልክ እንዲያቀርቡ አድርግ።
መዝሙር 44 እና ጸሎት